UFEAFA

United Former Ethiopian Air Force Association

The sign of freedom and unity

International union

  ​   የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ  

  
የበረራ ትምህርት ቤት
  
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የበረራ ትምህርት ቤት በ፲፱፻፴፮ ዓ/ም በጥቁር አሜሪካውያን የተጀመረ ሲሆን አዲስ እና በዘመናዊ በሆነ መልኩ በ ፲፱፻፴፰  ዓ/ም  ስዊድናውያን ኃላፊነቱን ተቀብለው በደብረ ዘይት ከተማ ተቋቋመ ።
 የኢትዮጵያ አየር ኃይል ረዘም ያለ አኩሪ ታሪክ ያለው እና በአፍሪካ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈ ተቋም ሲሆን የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና አንድነት በማስከበር ለሰላም እና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ። የአገርን ድንበር ከማስከበር ባሻገር በርካታ ምሁራንን በተለያየ የሙያና የትምህርት መስክ በማሰልጠን ይህ ነው የማይባል ተግባር አከናውኗል።
የኢጣሊያ ጦር በሃፍረት ከተመለሰ በኋላ በ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በሻለቃ ሚሽካ ባቢቼፍ የሚመራ የበረራ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ተቋቋመ በመቀጠልም አሜሪካዊው አብራሪ ጃን ሮቢንሰን እና ሌሎችም የውጭ አገር አስተማሪዎች ትምህርት ቤቱን ተቀላቀሉ በዚህም የስልጠና ተቋም የዛሬው አየር ኃይል መሰረት ተጣለ።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በተለያየ ቦታ የቀይ መስቀል ፓይለት በመሆን ያገለግሉ የነበሩትን ቮን ሮዘንን በነበራቸው ቅርብ ግንኙነት እና ቅን አገልግሎት በቀይ መስቀል በኩል ማድረጋቸውን በመገንዘብ  የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ያቋቁሙ ዘንድ መረጧቸው ቮን ሮዘን ለመጀመሪያ ጊዜ አስራ ዘጠኝ ስዊድናውያን በመምህራንነት አምጥተው በ1930 ዓ/ም የበረራ ትምህርት ቤቱን ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ዘይት እንዲዛወር አደረጉ ።   
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ደረጃ የበረራ ትምህርት ቤት በ፲፱፻፴፰ ዓ/ም በደብረ ዘይት ሲጀምር ስዊድን ሰራሽ የሆኑ ሳብ ሳፋየር 91 ኤ እና 91 ቢ በተባሉ አስር የማሰልጠኛ አውሮፕላኖችን ነበር ። በመጀመሪያው የበረራ ስልጠና በርካታ አደጋዎች በመድረሳቸው አዲስ በራሪዎችን ለመመልመል አስቸጋሪ ሁኔታ የተፈጠረበት አጋጣሚ የሚዘነጋ አይደለም ለዚህም እንደመፍትሄ የተወሰደው በመካኒክነት ተመልምለው በስልጠና እና በስራ ላይ ተሰማርተው ከሚገኙት መሃከል ፍላጎትና ብቃት ያላቸውን መመዘኛ ፈተና እና የጤና ምርመራ በማድረግ በብቃት ያለፉትን ማሰልጠን ተጀመረ በምሳሌነት ለመጥቀስ ያህል ጄነራል ዮሃንስ ወልደማሪያም ፤ ጄነራል ፋንታ በላይ ፤ ጄነራል አምሃ ደስታ ፤ ጄነራል ተጫነ መስፍን እና ሌሎችም ይገኙበታል ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በተለያየ የሙያ መስክ በአገር ውስጥ ሙያተኞችን ከማሰልጠን አልፎ አፍሪካውያን ወጣቶችን በማሰልጠን የአቪየሽን ጥበብ በአፍሪካ እንዲስፋፋና እንዲያድግ የበርካታ አገር ዜጎችን አሰልጥኗል ከነዚህም ውስጥ የኬኒያ ፤ የሱዳን ፤ የታንዛኒያ ፤ የኡጋንዳ ፤ የናይጄሪያ ፤ የደቡብ አፍሪካ ፤ የዛምቢያ እና የዚምባቡዌ ዜጎች የገኙበታል ከነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ በሃገራቸው የአየር ኃይል አዛዥ እና የሲቪል አቪየሽን እንዲሁም የአየር መንገድ ኃላፊ እስከመሆን ደርሰዋል ። የደቡብ የመን አየር ኃይል በ፲፱፻፹ዎቹ  መገባደጃ ላይ ፓይለቶቹ እና የጥገና ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የበረራ እና የቴክኒክ ትምህርት ቤት ስልጠና ያደርጉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ።    
  

 
  የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና አየር መንገድ ግንኙነት

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የአየር ኃይል አዛዥ መኮንኖች የቦርድ  አባል መሆን የጀመሩት የስዊድን መንግስት ለኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዦችን ከአገሩ በሚያስመጣበት ወቅት ነበር የመጀመሪያው የቦርድ አባል በመሆን ጄነራል አሰፋ አየነ አገልግለዋል። ከ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ጀምሮከውጭ ይመጡ የነበሩ አብራሪዎችን አስቀርቶ የአየር ኃይል አብራሪዎችን ወደ አየር መንገድ በመላክ ሙሉ በሙሉ ከአሜሪካኖች ከተረከቡ በኋላ በዋና ስራ አስኪያጅነት በመምራት የራሱ የሆነ የበረራ እና የቴክኒክ ትምህርት ቤት በማቋቋም ሙያተኞችን በዝውውር በመውሰድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ እንዲደርስ መሰረት ሆኗል ።
ከዚህ ፈታኝ ጦርነት በኋላ ዘመናዊ የሆኑ ፈጣን ተዋጊ ጀቶችን ከሶቪየት ህብረት በመግዛት የአየር ድንበራችን ዳግም በጠላት እንዳይደፈር እንዲሁም ከውስጥ ከተነሱ ጸረ አንድነት ኃይሎች ጋር እስከ መጨረሻው ድረስ ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲያደርግ ቆይቷል ።        
  
Place title here
You can edit text on your website by double clicking on a text box on your website. Alternatively, when you select a text box a settings menu will appear. Selecting ‘Edit Text’ from this menu will also allow you to edit the text within this text box.
You can edit text on your website by double clicking on a text box on your website. Alternatively, when you select a text box a settings menu will appear. Selecting ‘Edit Text’ from this menu will also allow you to edit the text within this text box. 
 
Add Your Title Here
Add Your Sub-Title Here
This area is fully editable and gives you the opportunity to go into more detail about your business, what you do and what sets you apart from the competition. This area is fully editable and gives you the opportunity to go into more detail about your business, what you do and what sets you apart from the competition his area is fully editable and gives you the opportunity to go into more detail about your business, what you do and what sets you apart from the competition.
Button